የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በ2015 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2015
የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በ2015 በጀት ዓመት ከዚህ በታች ከሎት-1- እስከ ሎት-2 የተዘረዘሩ የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን የተጫራቾች መመሪያ ማክበር አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው ፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ በግልጽ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር የሚያሳይ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) ብቻ በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ቅዳሜ ፣ ዕሁድና የበዓል ቀናትን ሳይጨምር በሚቆጠር እስከ 10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በሆስፒታሉ የግዥና ዕቅድ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 9 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማህተም ተደርጎ ፣ በየሎቱ ለየብቻ ተለይተው ኦሪጅናልና የማይመለስ ኮፒውን በመለየት የሚቀርብ ሆኖ ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ወይም እስከ 11ኛው ቀን 5፡00 ድረስ ግዥ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ቡድኑ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡10 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ (በዚሁ ዕለት) በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ቡድኑ ይከፈታል።
- ለሎት-1 ግዥዎች ላይ ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ በብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) እስከ ሎት-2 ባሉት ግዥዎች ላይ ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ በብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ስም የተዘጋጀ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ አቅርቦት አገልግሎት ግዥ ላይ አሸናፊዎች የሚያቀርቡት ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን የሆስፒታሉ ቴክኒክ ኮሚቴ በየጊዜው አቅርቦቱን ሲመጣ አይቶና ተቆጣጥሮ ይረከባል፤ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ተመላሽ ያደርጋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ በተጠየቀው መሰረት ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆኑን እና አለመሆኑን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ በመለየት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ሳምፕል በሚቀርቡባቸው ዕቃዎች ላይ ሆስፒታሉ ባዘጋጀው ስፔስፊኬሽን መሠረት የቴክኒካል ግምገማ ስለሚደረግ ተጫራቾች ይህንን በትክክል አይተውና ተገንዝበው ሳምፕል በማቅረብ እና ቴክኒካል መስፈርቱን በማየት መጫረት (ዋጋ ማቅረብ) ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሀሳብ ካላቸው ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሆስፒታሉ የግዥ ዕቅድ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት በጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊዎች ተለይተው ውል እስኪፈጸም ድረስ እንደተያዘ ይቆያል።
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ከ7 ቀን በኋላ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) (ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ስም የተዘጋጀ በማስያዝ በሰባት ቀን ውስጥ ውል ተዋውለው በጨረታ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የዕቃዎች የመጓጓዣ የትራንስፖርት ወጪ ጨረታውን ባሸነፈው ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል።
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ማንኛውም ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል።
- የጨረታውን 20% መጨመርና መቀነስ ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ላይ መሳተፍ የሚችለው በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ብቻ ሲሆን ከዘርፉ ውጪ የሆነ ተጫራች በጨረታው ሂደት የማይካተት ይሆናል። ሆስፒታሉ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 011- 515 -02- 42 በመደወል መረዳት ይቻላል።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቂርቆስ ክ/ከተማ ፍል ውሃ አጠገብ ገባ ብሎ ይገኛል።
የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል
