የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎችን እና መለዋወጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ግ.ጨ.ቁ. 44/2015
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ክዚህ በታች የተጠቀሰውን አቅርቦት ፍላጎት ካላቸው የሃገር ውስጥ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- Electro Mechanical and its accessories
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- ቫት ተመዝጋቢ
- ታክስ ክሊራንስ
- የግዥ ኤጀንሲ የምዝገባ ማስረጃ
- የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት
- በዘርፉ የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ወረቀት
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ90 ( ዘጠና ) ቀናት
- የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 100,000.00 ( መቶ ሺህ) ብር ሆኖ የጨረታ ማስከበሪያው በሲ.ፒ.ኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና መሆን ይኖርበታል።
- ሰነድ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ሰነዱ በሚገኝበት በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና መስሪያ ቤት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 01 የማይመለስ 300.00(ሶስት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ።
- የጨረታ ማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን እና ሰዓት 07 / 09 / 2015 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት
- ጨረታው የሚከፈተው፡- በዕለቱ 07 / 09 / 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ እና ማብራሪያ ዋናው መስሪያ ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 0114171703 መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡-
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ (ዋና መስሪያ ቤት ቱሉ ዲምቱ)
