የአጣየ ክ/መ/ሰ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ በስተኩርቲ በኩል ያለውን በግምት 2500 ካሬ ሜትር ላይ የሚገኝ ባህር ዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንግስት በሰ/ሽዋ ዞን በኤ/ግ ወረዳ የአጣየ ክ/መ/ሰ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ በስተኩርቲ በኩል ያለውን በግምት 2500 ካሬ ሜትር ላይ የሚገኝ ባህር ዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡_
- የጨረታ ማስከበሪያ የባህር ዛፍ ሽያጭ 10,000 (አስር ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ማሲያዝ እንደሚጠበቅባቸው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፅ/ቤታችን ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብራችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል።
- በጨረታ መክፈቻ ወቅት እንዲገኙ አይገደዱም ነገር ግን በጨረታው መገኘት አለብን ብለው ካሰቡ መገኘት ያለበት አካል የተጫረተው ባለቤት ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው አካል ኦርጅናል የውክልና ማስረጃውን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- ጨረታው ከወጣበት ከ29/7/2015 እስከ 13/8/2015 ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ማለትም በ14/8/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ 4:00 ሰዓት ይከፈታል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ተጫራቾች ለወሰዱት የተጫራች መመሪያ/የጨረታ ሠነድ/በእያንዳንዱ ገፅ የድርጅታቸውን በማህተም ሥምና ፊርማ በማድረግ መመለስ ይጠበቅባቸዋል።
- ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ውድድሩ የሚካሄደው በጠቅላላ ድምር ከፍተኛ ዋጋ ያመጣ ይሆናል።
- የጨረታው መነሻ ዋጋ 550,000 (አምስት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) ብቻ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል።
በሰ/ሽዋ ዞን በኤ/ግ ወረዳ የአጣየ ከ/መ/ሰ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
