የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አስተዳድር የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ፣ የመኪና ጎማና ዲኮር እና የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አብክመ/የመ/ል/ድ/አስ/
ብግጨ/01/2015
የአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አስተዳድር የፑል ተጠቃሚ ለሆኑ የመንግስት ልማት ድርጅት አስተዳድር ለቢሮ መገልገያ የሚሆን
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
- የመኪና ጎማና ዲኮር
- የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጠሪ መ/ቤቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30.00 (ሠላሳ ብር) በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ምድቦች /ሎቶች/ 1% ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ወይም የሚያስይዙት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ የተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
- ለተጠቀሱት ዕቃዎች ተጫራቾች የቴhኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከአንድ ቴክኒካል እና ከአንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ቴክኒካል እና አንድ ቅጅ ፋይናንሻል በጥንቃቄ በታሸ ፖስታ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ በግዥና ንብ/አስተ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብhመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አስተዳደር በግዥ ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን
- መ/ቤቱ ተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር: 058 320 1063 ፋክስ 058 320 1183 ፖ.ሳ.ቁ 965 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አስተዳደር
