የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በማዕቀፍ ስምምነት (በ2 ዓመት በሚቆይ የውል ጊዜ) ምድብ አንድ በሶስተኛ ወገን የሚከናወን የከባድ ተሽከርካሪ የማሽኒንግ ስራዎች (Outside Machining) እና ምድብ ሁለት የኢንጄክሽን ፖምፕ እና ኢንጄክሽን ኖዝል ጥገና የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር NCB/GOV/AAWSA/N-C-S001/2015
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በማዕቀፍ ስምምነት /በ2 ዓመት በሚቆይ የውል ጊዜ/ ምድብ አንድ በሶስተኛ ወገን የሚከናወን የከባድ ተሽከርካሪ የማሽኒንግ ስራዎች (Outside Machining) እና ምድብ ሁለት የኢንጄክሽን ፖምፕ እና ኢንጄክሽን ኖዝል ጥገና የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት መገናኛ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት ምድር ቢሮ ቁጥር 113 በመገኘት ከላይ ለተጠቀሰው ግዥ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በመንግስት የግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በዘርፉ በዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድረ-ገፅ የተመዘገበ ፣ ለዘመኑ ሕጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ በመወዳደሪያ ኤንቨሎፑ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- በጨረታው ለመሳተፍ ለምድብ አንድ ብር 75,000.00 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/ ለምድብ ሁለት- ብር 50,000.00 /ሃምሣ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢያንስ ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል። ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ሠነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- የተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ለሁለት ዓመት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት። ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።
- የጨረታ ሠነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
- ጨረታው ሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት 4ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳዳሪያ ሠነድ ተቀባይነት የለውም።
- ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት። ይህንን ያልገለፀ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጐ ይቆጠራል።
- ገዥው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን ዕቃዎች በ20% የመጨመር ወይም በ20% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የባለስልጣን መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- መገናኛ ከሚገኘው በተለምዶ 24 ቀበሌ የገቢዎች ሚኒስቴር አጠገብ ያለው ሰማያዊ ህንጻ ምድር ቢሮ ቁጥር 113
ስልክ ቁጥር ፡- 011 663 0857/011 662 0010
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
