ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የእሳት አደጋ ማጥፊያ (ሃይድራንት ሲስተም) መሳሪያ ዝርጋታ ለማሰራት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በድጋሚ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን የእሳት አደጋ ማጥፊያ /ሃይድራንት ሲስተም/መሳሪያ ዝርጋታ ለማሰራት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በድጋሚ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የእቃ አቅራቢዎች ምዝገባና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ፣ በሚፈለገው የሥራ ዘርፍ ተዛማጅ የሥራ ልምድ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የእለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 200.00 ከፍለው በመግዛት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንጻ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች የፋይናንሻልና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው። ጨረታው በ24/8/2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ /ከላይ የተገለጹ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶችን የጨረታ ማስከበሪያ ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅች 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሰነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ስልክ ቁጥር 011 155 5230
ድረ ገጽ (www.ethbspe.org )
Berhanena Selam Printing Enterprise
አዲስ አበባ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
