ዲጅታል ኦፖርቹኒቲ ትረስት ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች እና ፕሪንተር በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ዲጅታል ኦፖርቹኒቲ ትረስት በካናዳ የተመሰረተ አለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ተመዝግቦ በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ. |
የዕቃ ዓይነቶች |
መግለጫ |
ብዛት |
|
1 |
Desktop Computer |
|
15 |
|
2 |
ፕሪንተር |
|
15 |
በመሆኑም ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን የዕቃ ዓይነቶች የአንዱን ዋጋ በግልጽ በማስቀመጥ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ 22 ካፒታል ሆቴል ጀርባ GMA ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ በመምጣት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው የዕቃ ዓይነቶች በትንሹ የአንድ አመት ዋስትና መስጠት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም መጋቢት 27/2015 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 11/2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት 10 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በዕለቱ 11:00 ሰአት ላይ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሆኖ በሚቀጥለው ቀን ማለትም ሚያዚያ 12/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የባንክ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህ የባንክ ሲፒኦ አሸናፊ ተጫራች ንብረቶቹን ሙሉ በሙሉ ገቢ ሲያደርግ ወዲያውኑ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።
- የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ንብረቶችን ለድርጀታችን ማስረከብ ይጠበቅበታል።
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው እና በሰዓቱ ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመስረዝ መብት አለው።
011-667-3259
ዲጅታል ኦፖርቹኒቲ ትረስት
