Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Apr 2023, 11:20 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የጂብሰም ቦርድና ፓውደር ማምረቻ ማሽኖች እና ተያያዥ ዕቃዎች ግንባታዎች ፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና ተሽከርካሪዎች ፣ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ግንባታዎች ፣ የኤሌክትሪክ ስራዎች ፣ ማሽነሪዎችና መሣሪያዎች ፣ ተሽከርካሪዎች ግብዓቶችና የተጠናቀቁ ምርቶ ች፣ የጥጥና ሽንኩርት የመስኖ እርሻ ልማት ፣ ግንባታዎች ፣ ማሽነሪዎችና የለማ መሬት በሐራጅ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል


የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰጠው ብድር አመላለስ ዋስትና የያዛቸውና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90, 216/1992 እና 1147/11 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሐራጅ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው/መያዣ ሰጪው ሥም

የንብረቱ አድራሻ

የንብረት ዝርዝር

የቦታው ስፋት

የሐራጁ መነሻ ዋጋ በብር

የሐራጁ ደረጃ

ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ስዓት

1

ፋሙ ኢንዱስተሪያል ኃ/የተ/ግ/ማህበር

ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ሰሜን ሸዋ ዞን ወጫሌ ወረዳ፣ ሙከጡሪ ከተማ፣ ጎራ ከተባ ቀበሌ

የጂብሰም ቦርድና ፓውደር ማምረቻ ማሽኖች እና ተያያዥ ዕቃዎች ግንባታዎች፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና ተሽከርካሪዎች

4.791 % ሄ/ር (የማምረቻ ቦታ) እና 2000 ሄ/ር (የኳየሪ ቦታ)

ብር 63,248,963.49 (ስልሳ ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ አርባ ስምንት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሶስት ብር ከአርባ ዘጠኝ ሳንቲም)

ሁለተኛ

ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት

2

ኤም ኤን ኤስ ማኑፋክተሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

በኦሮሚያ ብሔራዊ

ክልላዊ መንግስት ፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ

የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ግንባታዎች፣ የኤሌክትሪክ ስራዎች፣ ማሽነሪዎችና መሣሪያዎች፣ ተሸከርካሪዎች ግብዓቶችና የተጠናቀቁ ምርቶች

106,638.95 ካሬ ሜትር

ብር 2,306,801,435 60 (ሁለት ቢሊዬን ሶስት መቶ ስድስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አንድ ሺህ አራት መቶ ሰላሳ አምስት ብር ከስልሳ ሳንቲም)

ሁለተኛ

ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00-6:00

 

3

ጂ.ጂ.ኤፍ ኢንትግሬትድ ፕሮዳክሽን ፋርም ኃ/የተ/የግል ማህበር

በሶማሌ ብ/ክ/መ/፣ሸበሌ ዞን፣ አዳድሌ ወረዳ፣ ጃሬ ቀበሌ

የጥጥና ሽንኩርት የመስኖ እርሻ ልማት፣ ግንባታዎች፣ ማሽነሪዎችና የለማ መሬት

300 ሄክታር

 

ብር 11,951,074.5 (አስራ አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃምሳ አንድ ሺህ ሰባ አራት ብር ከሃምሳ ሳንቲም)

ሁለተኛ

ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከጥዋቱ 4:00-6:00

 

ማሳሰቢያ፦

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 25 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡ በተጨማሪም ድርጅቱ ድጋሚ ለሐራጅ በሚቀርብበት ጊዜ ባንኩ ለሚያወጣው ወጪና ለሚደርስበት ኪሳራ ይጠየቃል።
  3. ሐራጁ የሚካሄደው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው' ተበዳሪው እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ተወካዮች ብቻ በተገኙበት በንብረቱ አድራሻ ይሆናል
  4. በሐራጁ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወዲያው ተመላሽ ይደረጋል።
  5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ክፍያዎችን የስም ማዛወሪያ ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
  6. የኤም ኤን ኤስ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፕሮጀክት የምርት ስራ ያልተቋረጠ በመሆኑ አሸናፊው ከግዢው ዋጋ በተጨማሪ በመጓጓዝ ወይም በክምችት ላይ ያሉ ጭማሪ ግብአቶች/ጥሬ ዕቃዎች/ እና በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ያለቁ ምርቶችን በርክክብ ወቅት በሚደረስበት የትመና ዋጋ መሰረት በጥሬ ገንዘብ /በዱቤ/ ከፍሎ መውሰድ አለበት።
  7. የፕሮጀክቱ የምርት መሣሪያዎች ተሽከርካሪዎች ወዘተ ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ናቸው። በመሆኑም የጨረታው አሸናፊ ከተበዳሪው ጋር ተመሳሳይ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ያለው ሊሆን ይገባል። አልያም የሚጠበቅበትን የመንግስት ቀረጥና ታክስ ይከፍላል።
  8. ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊስ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና ፕሮጀክቱን የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል።
  9. ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክት እና አኳየርድ አሴት ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-552-2469 ደውሎ ማግኘት ይቻላል። ንብረቱን መጐብኘት የሚፈልጉም ካሉ ከዳሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል።
  10.  ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሐራጁን በhፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

Save Tender