የአበባ ግደይ ቢዝነስ ግሩፕ የድርጅታዊ መዋቅርና የሰው ኃይል ሁኔታ እና የአመራር ማጎልበቻ ዘዴ ጥናቶችን በ3 ወር ጊዜ ውስጥ የሚያካሄድ የአማካሪ ድርጅት ወይም የባለሙያዎች ቡድን በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የአበባ ግደይ ቢዝነስ ግሩፕ የተሠማራባቸውን የግብርና የትራንስፖርት አገልግሎት እና የንግድ የቢዝነስ ዘርፎች በተወዳዳሪነት ለማስፋፋት እና ለማሳደግ ያዘጋጀውን የ5 ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዱ፡
የድርጅታዊ መዋቅርና የሰው ኃይል ሁኔታ፣
- የሥራ ዝርዝር መግለጫ፣
- የሠራተኞች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም
የአመራር ማጎልበቻ ዘዴ፣
ጥናቶችን በ3 ወር ጊዜ ውስጥ የሚያካሄድ የአማካሪ ድርጅት ወይም የባለሙያዎች ቡድን በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
በመሆኑም የጥናት ፕሮፖዛሉን እስከ ሚያዝያ4/2015 ዓ.ም ድረስ የሚያቀርብ ፣ በማኔጅመነት እና ተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ ማስትሬት ድግሪና በላይ ያላቸውን እና ተመሳሳይ ጥናቶችን ቢያንስ በሁለት ተቋማት ያካሄዱ ባለሙያዎች የሚመደብ ፣ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ያለው ፣ የወቅቱን የመንግስት ግብር የከፈለ የአማካሪ ድርጅት ወይም የባለሙያዎች ቡድን በጨረታው እንዲወዳደር እና የመወዳደሪያ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ ቄራ ፔፕሲ ፊት ለፊት ባለው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 እንዲያስገቡ የተጋበዙ ሲሆን ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው የማይገደድ መሆኑን ያስታውቃል።
ለተጨማሪ ማስረጃ የድርጅቱ ዌብሳይት www.abebagroup.com ይጎብኙ
