የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የበር የመስኮት እና የቁልፍ አቅርቦት ገጠማ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ግ.ጨ.ቁ. 34/2015
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን አቅርቦት ፍላጎት ካላቸው የሃገር ውስጥ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የበር የመስኮት እና የቁልፍ አቅርቦት ገጠማ አገልግሎት ግዥ
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- ቫት ተመዝጋቢ
- ታክስ ክሊራንስ
- የግዥ ኤጀንሲ የምዝገባ ማስረጃ
- የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት
- በዘርፉ የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ወረቀት
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ 60 ( ስልሳ ) ቀናት
- የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ብር ሆኖ የጨረታ ማስከበሪያው በሲ.ፒ.ኦ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- ሰነድ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ሰነዱ በሚገኝበት በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና መስሪያ ቤት በግዥ ክፍል ቢሮ. ቁጥር 01 የማይመለስ 300.00( ሶስት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ።
- የጨረታ ማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን እና ሰዓት 10 / 08 / 2015 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 9 00 ሰዓት
- ጨረታው የሚከፈተው በዕለቱ 10/ 08/ 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 9:30 ሰዓት
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ እና ማብራሪያ ዋና መስሪያ ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 011 417 1703 መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ (ዋና መስሪያ ቤት ቱሉ ዲምቱ)
