Tender Detail

Tender Details

  • Deadline19 Apr 2023, 1:09 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በማዕከላዊ/ጎ/ዞን የላይ አርማጭሆ ወረዳ ትክል ድንጋይ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ሲሚንቶ ፣ ቆርቆሮ ፣ ብረት ፣ የቆርቆሮ ሚስማር ፣ የኤሌክትሪክ እቃ ፣ መበየጃ ማሽንና የግብርና እቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ/ጎ/ዞን የላይ አርማጭሆ ወረዳ ትክል ድንጋይ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ግ/ፋ/አስ/ቡድን ለ2015 ዓ.ም በጀት አመት ለግንባታና ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ

  1. ሲሚንቶ ፣
  2. ቆርቆሮ ፣
  3. ብረት ፣
  4. የቆርቆሮ ሚስማር ፣
  5. የኤሌክትሪክ እቃ ፣
  6. መበየጃ ማሽንና
  7. የግብርና እቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡

  1. ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የ2015 ግብር የከፈሉ
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
  3. ተጫራቾች በወረዳው ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  4. የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ዋናውና ቅጅ ተለይቶ በሁለት ኮፒ ታሽጎ መቅረብ አለበት።
  5. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሰነዱን በላይ አርማጭሆ ወረዳ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን ገንዘብ 1 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጨረታ መክፈቻ እለት በፖስታው ውስጥ ታሽጎ ማስገባት አለባቸው።
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላሉ። የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለበትና ለመሰረዙ ልዩ ፊርማ ከሌለበት ውድቅ ይደረጋል።
  8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዚያውን ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል።
  9. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በጠቅላላ ድምር ነው።
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ማወዳደሪያ ሰነድ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው።
  11. አሸናፊው ተጫራቾች ንብረቱን ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ድረስ በራሳቸው ወጭ አምጥቶ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው።
  12. አሸናፊው ተጫራች ኦርጅናል ያልሆነ እቃ ቢቀርብ ውሉ የሚሰርዝ መሆኑንንና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ መሆኑንን ማወቅ አለባቸው።
  13. ጨረታው ሙሉ ወጭን ያካተተ ነው።
  14.  የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ብሔራዊ በዓልና እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
  15. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋችሁ በስልክ ቁጥር 058 116 0838 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡ ኮሌጅ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የትክል ድንጋይ/ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ

Save Tender