ወገን የበጎ አድራጎት ማኅበር አዳማ የሂሣብ መዝገቡን በታወቀ የውጪ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል
የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
ወገን የበጎ አድራጎት ማኅበር አዳማ የሂሣብ መዝገቡን በታወቀ የውጪ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ከታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማለትም፡_
- የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው፤
- የታደሰ የሥራ ፈቃድ ያለው፤
- የዓመቱን የሥራ ግብር የከፈለ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፤
- ከዋናው ኦዲተር የታደሰ ፈቃድ ያለው አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።
ከላይ የተዘረዘረውን ስፈርት የሚያሟሉ ኦዲተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዳቸውን ፎቶ ኮፒውን በመያዝ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
አድራሻ፡- አዳማ ከተማ ቀበሌ 04
ወገን የበጎ አድራጎት ማኅበር /አዳማ/
