Tender Detail

Tender Details

  • Deadline18 Apr 2023, 12:38 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Firewood

የምስ/ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በ2015 የበጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ለምግብ ማብሰያ አገልግሎት የሚውል የማገዶ እንጨት ለ6 ወር በግልጽ ጨረታ ከህጋዊ ነጋዴዎችን አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት መግዛት ይፈልጋል


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የምስ/ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በ2015 የበጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ለምግብ ማብሰያ አገልግሎት የሚውል የማገዶ እንጨት ለ6 ወር በግልጽ ጨረታ ከህጋዊ ነጋዴዎችን አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት የምንፈልገው አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር ይገኛል። እንዲሁም ህጋዊ ነጋዴዎች ማሟላት የሚገባቸው፡

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው ለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ጨረታው ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ሽያጭ ለሚፈፅሙ አቅራቢዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ።
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ድረስ በስራ ሰዓት ምስ/ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ከገንዘብ ያዥ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ በስራ ፈቃዳቸው መሰረት ማቅረብ የሚገባቸውን የዕቃ ዓይነቶች ለይተው በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ በመምሪያው ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ለመወዳደር ባቀረቧቸው የዕቃዎች ገንዘብ መጠን የጨረታ ማሰከበሪያ 1 በመቶ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /በጥሬ ገንዘብ/ የሚያሲዙ ሲሆን አሸናፊው ውል ሲይዝ የውል ማሰከበሪያ በጨረታ ማስከበሪያ ላይ በመጨመር 10 በመቶ የሚያሲዝ ሆኖ የተሸነፈ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያው በመመሪያው መሰረት የሚመለስ ይሆናል።
  6. ጨረታው ከ10,000 /አስር ሺህ ብር/ በላይ ለሆነ ግዥ ከሚከፈለው ጠቅላላ ገንዘብ ላይ በመመሪያው መሰረት 2 በመቶ የሽያጭ ታክስ (ቅድመ ግብር ክፍያ) መክፍል ይኖርበታል።
  7. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  8. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ወቅት ዋጋ የሞሉበት ሰነድ ላይ ፊርማና የድርጅታቸውን ማህተም ማሳረፍ አለባቸው።
  9. የጨረታ አሸናፊዎች ውጤቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል ይዘው ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ማረሚያ ቤቱ ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. የጨረታው ሳጥን የሚታሸግበት ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀን ከቀኑ 11፡30 ታሽጐ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል።
  11. የጨረታ መክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  12. መምሪያው ጨረታውን አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 771 1636 ደውለው ወይም በአካል ምስ/ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ።

የምስ/ጐጃም ዞን ማረ/ቤቶች መምሪያ

Save Tender