በምዕ/ጎጃም ዞን የይ/ዴ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለይ/ዴ/ወ/ግብርና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚዉሉ በሞሰቦ ቀበሌ የሚገኝ በመንደረጌሱስ ጎጥ ችግኝ ጣቢያ የደን ሽያጭ ማለትም ባህር ዛፍ ፣ ግራቢሊያ ፣ የፈረንጅ ጥድ እና የተለያዩ ዛፎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕ/ጎጃም ዞን የይ/ዴ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለይ/ዴ/ወ/ግብርና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚዉሉ በሞሰቦ ቀበሌ የሚገኝ በመንደረጌሱስ ጎጥ ችግኝ ጣቢያ የደን ሽያጭ ማለትም
- ባህር ዛፍ ፣
- ግራቢሊያ ፣
- የፈረንጅ ጥድ እና
- የተለያዩ ዛፎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛዉም ተጫራች መሳተፍ እንደሚችሉ እየጋበዝን መስፈርቶችም፡
- የቲን ተመዝጋቢ መሆናቸዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በዘርፉ አግባብ ያለዉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ግዥው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ ማስረጃ ቢያስፈልጋቸዉ የይ/ዴ/ወ/ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ወይም በስልክ ቁጥር 058 338 0298 ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ሂሳብ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከዋና ገንዘብ ያዥ አስይዘዉ ለግዥ ኦፊሰሮች ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል። በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከሆነ ከፖስታ ዉስጥ አስገብተዉ ማሸግ ይችላሉ።
- የጨረታ አሸናፋዎች ከጠቅላላ ዋጋ 13 በመቶ ሮያሊቲ ክፍያ ለይ/ደ/ወ/ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት የሚከፍሉ ሲሆን ደኑን ለመግዛት ያሸነፉበትን ዋጋ በአንድ ጊዜ ከፍዉ ደኑን ማንሳት የሚችሉ።
- ሁሉንም ደን ቀጭን ወፍራም ሳይባል በጅምላ መግዛት የሚችሉ።
- ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ካለ ከአሸናፊዉ ዋጋ ጋር ተደምሮ ሲያዝ የተሸነፈዉ ተጫራች የሚያስይዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
- ጨረታዉ የሚከፈትበት ዕለት በበዓል ቀናት ከሆነ ወደ ቀጣዩ የስራ ቀን ይሸጋገራል።
- የጨረታ ሰነዱን ከ25/07/2015 ዓ.ም እስከ 15/08/2015 ዓ.ም ለ21 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የተሞላበትን ፎርም ቲን ፣ የንግድ ፈቃድዎንና ሌሎች ያልተጠቀሱ ማስረጃዎችን በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታዉ የሚዘጋበት 16/08/2015 ዓ.ም በ3፡30 ሲሆን ጨረታዉ የሚከፈተዉ 16/08/2015 ዓ.ም በ4፡00 ቢሮ ቁጥር 3 ፍላጎት ያላቸዉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በጨረታዉ መክፈቻ ዕለት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታዉን ለመክፈት የሚገድበዉ የለም።
- አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች አሽገዉ ከሚያስገቡት ሰነድ እና ፖስታ ላይ አድራሻና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት።
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ጨረታዉን የምናወዳድረዉ በሎት /በጠቅላላ/ ዋጋ ነዉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
- የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ታክስ ያካተተ መሆን አለበት።
- ጨረታዉ ለ40 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
- የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ነዉ።
የይልማና ዴንሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት
