Tender Detail

Tender Details

  • Deadline18 Apr 2023, 12:24 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Equipment And Accessories

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ንብረት አስተዳደር ቡድን በዞኑ ስር ለሚገኙት መምሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችንና የፈርኒቸር እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ንብረት አስተዳደር ቡድን በዞኑ ስር ለሚገኙት መምሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1 የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችንና
  • ሎት 2 የፈርኒቸር እቃዎችን ለ2ኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። 

ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው

  1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃዽ ማረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተዘገቡ ሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንከ በተረጋገጠ የፍያ ትዕዛዝ |ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንh ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ መሂ , በማስያዝ ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ለግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖሊታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም የሚያስይዙት ዋስትና ከ በመቶ ቢያስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከሰ/ጎ/ዞን/ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የተሞላበት ሳይኖረው ኦርጂናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰሜን ጎንደር ዞን አሰተዳደር ደባርቅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይቻላል።
  7. ጨረታው በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከ 25/07/2015 እስከ 09/08/2015 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር | በቀን 10/08/2015 ዓ.ም በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 የከፈታል።
  9. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን የኤሌክትሮኒክስ እና የፈርኒቸር እቃዎችን ግዥዎች የሚያቀርበው ለሰ/ጎ/ዞን ባሉት ንብረት ክፍል ይሆናል።
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው የጨረታ ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ወይም በነጠላ ዋጋ መቤቱ የተሻለ አማራጭ የሚወስድ ይሆናል።
  11. የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  12. መስሪያ ቤቱ ይህንን ጨረታ ከላይ በሎት ከ1–2 በተገለፁት መሰረት የተዘረዘሩትን ግዥዎች የተሻለ አማራጭ ካገኘሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 1 ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 817 0040 መጠቅ ይችላሉ።

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ

 

Save Tender