የስማዳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለጸዶየ ጤና ጣቢያ እና ለአርያት ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውል የማስፋፊያ ግንባታ በዲዛይኑ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የስማዳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን በ2015 በጀት ዓመት በጤና ሚኒስተር ፣ በክልሉ ጤና ቢሮ እና በወረዳው የጣምራ በጀት በስማዳ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ
- ለጸዶየ ጤና ጣቢያ እና ለአርያት ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውል የማስፋፊያ ግንባታ በዲዛይኑ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ግንባታው ማንኛውንም ወጭ ማቴሪያልን ጨምሮ በጨረታ አሸናፊ የሚሸፈን ይሆናል።
በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት የሚፈለግባቸው መስፈርቶች፡
- ህጋዊ |ወቅታዊ/ የታደሰ በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቲን ካርድ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን እና ሌሎች መረጃዎቻቸውን በፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 2 ተከታታይ ቀናት በስማዳ ወረዳ ግ/ፋን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 27 ለሥራው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ታስቦ በ22 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3:30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ስማቸውን ፣ ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን እንዲሁም ማህተማቸውን ማስፈር አለባቸው።
- የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ |ማሻሻያ| ማድረግ እና ከጨረታው እራሣቸውንችሉም።
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ እና ለወደፊቱም በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሠነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ስ/ወ/ገ/ያዥ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 1 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በዋና ገንዘብ ያዥ ማስያዝ እና ያስያዙበትን ኮፒ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖረባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ በዋና ገንዘብ ያዥ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው። ይሁን እንጅ አርቲሜቲክ ቸክ ሲሰራ ከመሀንዲስ ግምቱ ከተቀመጠው ዋጋ በታች 25 በመቶ ዝቅ ብሎ የሞላ ተጫራች የውል ማስከበሪያ 25 በመቶ ያስይዛል። አሰሪ መ/ቤቱ ካመነበት ውል ይወስዳል የቅድሚያ ክፍያ አይፈቀድለትም።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው ተጫራቾች |ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- የአሸናፊ ጥሪ ማስታወቂያ ከጨረታ ሰነዱ ከሰነዱ ላይ ባስቀመጣችሁት ስልክ ቁጥር የምናሳውቅ እና በተጨማሪም በአካባቢ ማስታወቂያ ስለሚገለጽ ተከታትለው ውል መውሰድ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ተነባቢ የሆነና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት። ስርዝ ድልዝና ተነባቢነት ከሌለው ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ።
- ተወዳዳሪዎች ቢያንስ 3 እና ከዚያ በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5 በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ በላይ ልዩነት ያለው ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ።
- የግንባታ ዘርፉ ፈቃድ ያላቸውና ደረጃ 8 እና በላይ መወዳደር ይችላሉ።
- ለበለጠ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 058 667 0301 ደውለው ወይም ግ/ንአስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 27 በአካል ጠይቆ መረዳት ይቻላል።
የስማዳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
