በባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የብስ ትራንስፖርት ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት በ2015 በጀት አመት የሬኖና ሲ-ትራክ ከባድ ተሽከርካሪ መለዋወጫ ፣ የጋራዥ ዕቃዎችና መገልገያ መሳሪያዎችና የኮምፒተር ተዛማዥ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በድጋሚ የሬኖና ሲ-ትራክ ከባድ ተሽ/መለዋወጫ የጋራዥ ዕቃዎችና መገል/መሳሪያዎችና የኮምፒ/ተዛ/እቃዎች ግልፅ ጨረታ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ESL/KIB/04/2015
በባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የብስ ትራንስፖርት ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት በ2015 በጀት አመት
- ሎት1. የሬኖ ከባድ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- ሎት2. የሲኖ ትራክ ከባድ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- ሎት3. የጋራዥ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- ሎት4. የጋራዥ መገልገያ መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- ሎት5. የተለያዩ ኮምፒውተርና ተጓዳኝ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ካላቸው ከአገር ውስጥ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. በዚህ መሠረት ጨረታ ተካፋይ የሚሆኑ ተጫራቾች
1.1. የዘመኑን ግብር የተገበረበት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣
1.2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣
1.3. የግብር ከፋይነት /Tin Number/ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣
1.4. ተጫራቾች በመንግስት ንብረት ማስወገድ እና ግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ከቅ/ጽ/ቤቱ ግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 108 ቀርበው የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የነጠላ ዋጋ እና የጠቅላላ ዋጋ ተ.እ.ታን ያካተተ መሆኑን መግለጽ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ጨረታው ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት እና ጨረታው እስከሚከፈትበት እለት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
4.1.የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ጨረታ እንዲሁም የፋይናንሸል ሰነድ ኦርጂናል እና ኮፒ በማድረግና በታሸገው ኢንቨሎፕ ላይ የጨረታ ቁጥር ESL/KIB/04/2015 በመፃፍ ቅ/ጽ/ቤቱ የግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 108 በተጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
4.2 ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያሰሩት በባንክ የተረጋገጠ CPO ሆኖ Ethiopian Shipping and Logistics Services Enterprise Kality Branch Office በሚል መሰራት ይኖርበታል።
5. ጨረታው በ22ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 4፡30 ሰዓት በቅ/ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 102 የተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሳቸው ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ቀርበው ውል ማሰር ይጠበቅባቸዋል።
7. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ሳሪስ አቦ ቤተክርስቲያን አጠገብ ያለው የጉምሩክ ግቢ ውስጥ / የቀላል ባቡር ግቢ አጠገብ የድሮ ኮሜት ግቢ ውስጥ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 440 1498/40 4078
ኢ.ባ.ት.ሎ.ቃ.ቅ
