Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Apr 2023, 11:19 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Chemicals And Reagents

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ2015 ጂኦሎጂ እና የፊዚክስ ፣ የባዮሎጂ እና የኬሚስትሪ ፣ የአንስቲዥያ ላብራቶሪ የቤተሙከራ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር ድ/ዳ/ዩ/ግ/ጨ/7/9/10/2015

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ2015 ጂኦሎጂ እና የፊዚክስ ፣ የባዮሎጂ እና የኬሚስትሪ፣ የአንስቲዥያ ላብራቶሪ የቤተሙከራ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ህጋዊና ብቃት ያላቸውን የሀገር ውስጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

በዚህም መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፦

1 የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 9 ከተጠቀሱት አድራሻዎች ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በአካውንት ቁጥር 606C21002728 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስገብታችሁ ደረሰኝ በማምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

2- ተጫራቾች የጂኦሎጂ እና የፊዚክስ የቤተ ሙከራ እቃዎች (ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል) የጨረታ ሰነዳቸውን በሁለት የተለያየ የታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:15 ሰዓት ድረስ በተ.ቁ 9 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3- የጨረታው ሳጥን በዚሁ ዕለት እና ቦታ ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

4- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው አካተው መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው።

4.1. በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድ ሆኖ ለዘመኑ ስለመታደሱ የተረጋገጠ፤

4.2. ማንኛውም የወቅቱን የመንግስት ግብርና ታክስ ለመክፈላቸው ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣታቸው ማረጋገጫ፤

4.3. በመንግስት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ተጫራች ድርጅቶች የተጠቀሰውን ማስረጃ ሲያቀርቡ ማስረጃው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የተሰጠ ማስረጃ ብቻ መሆን እንዳለበትና በጨረታው መከፈቻ ዕለት የተሰጠ ማስረጃ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልፃለን።

4.4. የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸ የሚያረግጥ የምዝገባ ምስክር 9 ወረቀት፤

4.5. ተጫራቾች ዩኒቨርሲቲው ባወጣው የጨረታ ሰነድ ውስጥ በተጫራቾች የሚሞሉ ቅጾችን በትክክል ሞልተው በመፈረም እና ማህተም በማድረግ መመለስ ይጠበትባቸዋል።

4.6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከዚህ በታች በተገለፀው ሰንጠረዥ መሰረት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4.7. ከዚህም በተጨማሪ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋስትና የጨረታ ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት ቀን በኋላ ላሉት 28 ቀናት የዋስትናውን ሕጋዊነት የሚያረጋግጥ መሆን ይኖርበታል።

ተ.ቁ

የዕቃዎች መግለጫ

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

 

የጂኦሎጂ እና የፊዚከስ የቤተ-ሙከራ እቃዎች

 

1

Geological Field equipment

50,000.00

Nuclear lab

200,000.00

2

የባዮሎጂ እና ኬሚስትሪ ላብራቶሪ እቃዎች

30,000.00

3

የአንስቲዥያ ላብራቶሪ የቤተ-ሙከራ እቃዎች

50,000.00

 

5. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የስራ አፈፃፀም ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣ በተጨማሪም ተጫራቾች አቅርቦቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6.ዩኒቨርሲቲው የተጫራቾችን ብቃት ለማረጋገጥየሚያስችሉስፈርቶች የጨረታመመሪያዎችና ሌሎችም ተዛማጅነት ያላቸውን መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ያካተተ ስለሆነ በሁሉም ተሳታፊ ተጫራቾች እንዲተገበሩ ያሳስባል።

7- ተጫራቾች ስለ ማጭበርበር እና ሙስና ላለመፈፀም ማረጋገጫ በመስጠት ግዴታ የሚገባበትን ቅጽ በመፈረም ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8- ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

9- ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ድሬዳዋ ዩኒርቨሲቲ ቢሮ ቁጥር-4-2ተኛ ፎቅ ላይ

ስልክ ቁጥር 025 112 7863

ፋክስ ቁጥር 025 112 7971/77

ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1362

ድሬዳዋ ዩኒቭርስቲ

Save Tender