በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የንጹህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያና ቦኖ ግንባታዎች እና የመጸዳጃ ቤት ግንባታዎች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በአበሽጌ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ማ/ጽ/ቤት በ2015 ዓ.ም. ግንባታ ለመስራት በታቀደው መሰረት፤
- የላቼና ኦማንቾ ፣ የዳርጌ ከተማ ፣ የጣደሌ ፊቴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና የላይ ፈንጣ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የንጹህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያና ቦኖ ግንባታዎች ሎት 1 (አንድ)
- የላይ ፈንጣ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እና የቁሊት አንድ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የመጸዳጃ ቤት ግንባታዎች ሎት 2
- የጣዉላ ጤና ኬላ እና የዳርጌ ጤና ጣቢያ የመጸዳጃ ቤት ግንባታዎች ሎት3 (ሦስት) ግንባታዎችን ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
1. በሎት አንድ ጨረታ ለሚወዳደሩ ተጫራቾች ፈቃዳቸው WC/GC ደረጃ 7(ሰባት) አና ከዚያ በላይ፤
2. በሎት 2 እና 3 ለሚወዳደሩ ተጫራቾች ፈቃዳቸው BC/GC ደረጃ 7(ሰባት) እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶክመንታቸውን ዋናውንና አንድ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፉ የ2014/2015 ዓ.ም. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ፣ የግንባታ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ጊዜው ያላለፈበት ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (Copy) ይዘው በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በአበሽጌ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ማ/ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በፋ/ኢ/ል/ማ/ጽ/ቤት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች ለ60 ቀናት የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /BID BOND/ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ (unconditional Bank Guarantee) የማቅረብ ግዴታ አለበት። የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን በቴክኒካል ኦሪጅናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፣ ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም በሰም የታሸጉትን 6 ፖስታዎች በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማድረግ የድርጅቱን ማህተም እና የተወዳደሩበትን ሎት አይነትና ስም በመጻፍ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ከሆነ ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል።
- ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን ፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈር ማህተም ማድረግ እና ኤንቨሎፑን በሰም በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያው በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን በአበሽጌ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ማ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 8:00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጽ/ቤቱ ባወጣው የግንባታ ጨረታዎች ተጫራቹ ከአንድ ፕሮጀክት (ከአንድ ሎት) በላይ በጨረታ መሳተፍ አይችልም።
- ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8:30 ጀምሮ በአበሽጌ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ማ/ጽ/ቤት ይከፈታል።የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአበሽጌ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት ወይም በአበሽጌ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ማ/ጽ/ቤት በግንባር ወይም በአካል በመቅረብ መረዳት ይችላሉ።
በስልክ ቁጥር:- 011 330 2604 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ወልቂጤ
