የአ/አበባ ፖሊስ በ2015 በጀት ዓመት የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር AAPC NCB 0010/015 ዓ.ም.
የአ/አበባ ፖሊስ በ2015 በጀት ዓመት የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን፦
|
ሎት |
የጨረታ ዓይነት |
የናሙና መለያ |
የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን |
|
001 |
ቶዮታ ሪቮ ተሽከርካሪዎች ኬሪቦይ ግዥ |
በኮሚሽኑ ፍላጎት መሰረት |
15,000 |
ስለዚህ፡-ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሁፍ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና የታደሠ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለበት።
- አማራጭ ዋጋ እና አማራጭ ዕቃ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን (ፋይናሻል) ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውንም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን ዕቃ አይነት በትክክል በመፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን፣ ስርዝ ድልዝ፣ በፍሉድ የጠፋ፣ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲ.ፒ.ኦ. ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አ/አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ግምጃ ቤት ወይም በክፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
- በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መሰረት ይሆናል።
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ ያቀርቧቸው ዕቃዎች ኮሚሽኑ ባወጣው ፍላጎት መግለጫ መሰረት መሆኑን በኮሚሽኑ የጥራት ኮሚቴ ወይም ባለሙያ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን እስከ 4:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቃል።
- ተጫራቾች አራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ቤት ቢሮ ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 07 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ8ኛው ቀን እስከ ጠዋት 4:30 ሠዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በኮሚሽኑ ግዢና ፋይናንስ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- በጨረታ ሰነዱ ከፍል 2 ላይ በሚጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 5፡00 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 512 ይከፈታል።
- የጨረታው መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 4:30 ሰዓት ታሽጎ 5:00 ሲሆን ይከፈታል።
- ዘግይተው የሚጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር - 011 862 5800 (011 111 0448)
የአዲስ አበባ ፖሊስ
