የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት የድንች መላጫ (Potato Peeler) ፣ የበረዶ መፈልፈያ (Ice Maker) ፣ የእንቁላል መምቻ ማሽን (Egg Mixer Machine) ፣ የቡና ማሽን (Coffee Machine)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፀውን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት፦
ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ/አገልግሎት ግዥ
ሎት 1 የድንች መላጫ (Potato peeler)
- የበረዶ መፈልፈያ (Ice Maker)
- የእንቁላል መምቻ ማሽን (Egg mixer Machine)
ሎት 2 የቡና ማሽን (Coffee Machine)
- የቁም ፍሪጅ (Stand Frezer)
- ዲፕ ፍሪጅ (Deep Frezer)
- የፒዛና የኬክ መጋገሪያ (Pizza & Cake Oven/Maker/)
ሎት 3 ኮምፒውተሮች
- ፕሪንተር
ሎት 4 የላውንዳሪ ማሽን ጥገና
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2015 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስhር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች
- ለሎት 1፣2 እና 3 ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) እና
- ለሎት 4 ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር የሚገለጽ መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም። ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት። ሰለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይስረዛል።
- ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16/8/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ (Bid document) መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል። የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥን ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሂደቱ የቴhኒካል ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴክኒካል ሠነድ ግምገማና እስፔስፊኬሽን (Specification) ግምገማ ውጤት (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ። ነገር ግን ቴክኒካል ግምገማ ሰነድ ወይም እስፔስፊኬሽን (Specification) ግምıማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሰነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ። የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011 551 9100/0115 53 0767/011 515 7337
የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
