Tender Detail

Tender Details

  • Deadline19 Apr 2023, 10:57 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Chemicals And Reagents

በፌዴራል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ለወርክ ሾፕ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ፣ መካኒካል እና ሲቪል ወርክ ቁሳቁሶች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በፌዴራል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ለወርክ ሾፕ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ፣ መካኒካል እና ሲቪል ወርክ ቁሳቁሶች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡_

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤

2.የግብር መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፤

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 ብር (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቢሮው ግዥና ፋይናንስ የስራ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት የተለያዩ ሎቶች ከዚህ በታች በተመለከተው ሰንጠረዥ መሰረት ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች ማለትም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional bank guarantee) ወይም በጥሬ ገንዘብ በፌዴራል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ/Bahir Dar industry park በሚል ስም የተዘጋጀ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።

ተጫራቾች የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና Bid Bond) መጠን

ሎት ምድብ

የዕቃው ዓይነት

 

መለኪያ

ብዛት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የገንዘብ መጠን በብር

1

Mechanical hand tools and machine

በቁጥር

75 ዓይነት

10496

2

Civil work tools and equipment

በቁጥር

25 ዓይነት

1037

3

Electrical hand tools machines

በቁጥር

32 ዓይነት

2595

4

Disinfection system

laboratory equipment

በቁጥር

7 ዓይነት

9597

 

6.ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥና ፋይናንስ የስራ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7.ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ክፍት ሆኖ ቆይቶ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በቢሮው አድራሻ ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻው ቀን ህዝባዊ በዓል/ሳምንታዊ የስራ እረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተጠቀሰው ሰዓት የሚዘጋና የሚከፈት ይሆናል።

8 ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ለበለጠ ረጃ በስልክ ቁጥሮች 058 556 6818/0918 27 04 52 በመደወል ወይም በአካል በቢሮው ግዥና ፋይናንስ የሥራ ክፍል በመቅረብ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

በፌዴራል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ  

 

 

 

Save Tender