በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ-ኢትዮጵያ ኤርፖርቶች በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 2 ውስጥ በሚገኙ ባዶ ቦታዎች ላይ ከቀረጥ ነጻ የችርቻሮ ንግድ አገልግሎቶችን (Duty Free Retail Business) በገቢ መጋራት አሰራር (Concession Business Modality) መስጠት የሚፈልጉ ባለሀብቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- SSNT-371
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ-ኢትዮጵያ ኤርፖርቶች በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 2 ውስጥ በሚገኙ ባዶ ቦታዎች ላይ ከቀረጥ ነጻ የችርቻሮ ንግድ አገልግሎቶችን (Duty Free Retail Business) በገቢ መጋራት አሰራር (Concession Business Modality) መስጠት የሚፈልጉ ባለሀብቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡_
- በአገልግሎቱ ዘርፍ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፤ የTIN ምዝገባ ወረቀት ያለው፣ VAT ተመዝጋቢ የሆነ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ፤ አምስት (5) ዓመትና እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ሶስት መቶ ብር (300.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T371 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
- በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች 100,000 ብር (አንድ መቶ ሺ ብር ብቻ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል እስከ ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፓስ ቢሮ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፦
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር፦ 011-517-8953
ኢ-ሜይል: LimenihG@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
