Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Apr 2023, 10:36 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2015 ዓ/ም በጀት ዓመት ለአዳራሽ አገልግሎት የሚውሉ የአዳራሽ ወንበር ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


ለሁለተኛ ግዜ የወጣ የዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ (2015 ዓ/ም በጀት ዓመት ለአዳራሽ አገልግሎት የሚውሉ  ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ሊገዙ የተፈለጉ ዕቃዎች

  1. የአዳራሽ ወንበር

በመሆኑም ከላይ የተጠቀሰውን የአዳራሽ ወንበር ለመጫረት የሚትፈልጉ ተወዳዳሪዎች አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘተሩትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ጨረታውን ተወዳደሪ|አቅራቢ/ድርጅቶች የ2015 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ሆን ይጠበቅባቸዋል።
  2. የገንዘብና ኢኮ/ል/ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የአዳራሽ ወንበሩን ለአይነት ማቅረብ የሚችሉና መ/ቤት በአካል ቀርቦ ለማየት ከፈለገ ለመተባበር ፍቃደኛ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ዋጋውን ከቫት ውጭና ከነቫቱ በጥራት መሞላት ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ቫት ከተካተተበት ተካቶበታል ተብሎ፣ ያልተካተተ ከሆነ አልተካተተም ተብሎ ሊጻፍ ይገባዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ቫት እንደተካተተ አድርጎ መ/ቤቱ የሚወስድ መሆኑን እናሳውቃለን።
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጠቅላላ ዋጋ 1.5% ብር 11.925.00 የጨረታ ማስከበሪያውን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፤ ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስገባት አለባቸው።
  8. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከኮሌጁ ጋር ውል ተዋውለው የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ ያሸነፉበትን ዕቃ በ15 ቀናት ውስጥ ለኮሌጁ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። ይህ ሳይሆን ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት 10% በቀጥታ ለኮሌጁ ገቢ ሆኖ ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል።
  9. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን ጋዜጣው ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ይውላል። ተጫራቾች ከኮሌጁ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
  10.  ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ ማህተም አርፎበት በሰም በታሽገ ኤንቭሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  11. ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ታሽጎ ከቀኑ 9፡00ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 16ተኛ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ባለመገኘታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉለውም። ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለበለጠመረጃ ስልክ ቁጥር 046 331 3848 ወይም 046 331 2719 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Save Tender