የግብርና ሚኒስቴር ከስርአተ ምግብ ተኮር ግብርና አቅም ግንባታ ፕሮጀክት በሚሸፈን በጀት የተለያዩ ፈርኒቸሮች (የቢሮ እና የላብራቶሪ) ፣ የአይሲቲ (ታብሌቶች) ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎችና የኪችን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
1.የግብርና ሚኒስቴር ከስርአተ ምግብ ተኮር ግብርና አቅም ግንባታ ፕሮጀክት በሚሸፈን በጀት የተለያዩ ፈርኒቸሮች (የቢሮ እና የላብራቶሪ) ፣ የአይሲቲ (ታብሌቶች) ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎችና የኪችን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በተጨማሪም ለዚህ ግዥ የሚሆን በጀት አለው፡፡ የጨረታ ቁጥር የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀንና ሰዓት ፣ የጨረታ መግለጫ ፣ በግዥው ዓይነት እና አገልግሎቱ የሚፈለግበት ቦታ እንደሚከተለው ነው።
|
የጨረታ ቁጥር |
የሎት ቁጥር |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት |
|
ብ/ግ/ጨ-ግ/ሚ/001/2015
|
ሎት-01
|
የኪችን እቃዎች |
20,000.00 ብር |
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት
|
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ሰዓት
|
|
ሎት-02 |
የተለያዩ ፈርኒቸሮች (የቢሮ እና የላብራቶሪ) |
20,000.00 ብር |
|||
|
ሎት-03 |
የአይሲቲ (ታብሌቶች) |
10,000.00 ብር |
|||
|
ሎት-04 |
የኤሌክትሪክ እቃዎች |
5,000.00 ብር |
2. መስሪያ ቤቱ ብቁ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ግዥ የታሸገ የጨረታ ሰነድ እንዲያስረክቡ ወይም እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።
3. ጨረታው የሚከናወነው በግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በወጣው የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ መሠረት ነው።
4. ፍላጎት ያላቸው ብቁ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ሊያገኙ የሚችሉትና የጨረታ ሰነዶች የሚመረመሩበት ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 በተገለጸው አድራሻ ነው።
5. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጁ የተሟሉ የጨረታ ሰነዶችን እያንዳንዱ በነፃ ከዚህ በታች በቁጥር 7 በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የተጫራቹን ስም ለማስመዝገብና የጨረታ ሰነዱን ለመረከብ በሚቀርበው ተጫራች ወይም በተወካዩ አማካኝነት ይሆናል። መ/ቤቱ ለሰነዱ መጥፋት ወይም መዘግየት ኃላፊነት የለበትም።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 በተገለጸው አድራሻ ሚያዘያ 10/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ወይም ከዚያ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሁሉም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 1 ስር በሠንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ መጠን ለሚወዳደሩበት አገልግሎት በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ዋስትና ያቀርባሉ። ዘግይቶ የቀረበ ጨረታ ውድቅ ይደረጋል። ጨረታው የተጫራች ወኪሎች (በጨረታው ለመገኘት የፈለጉ) በተገኙበት በተራ ቁጥር 7 በተገለጸው አድራሻ ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 1 ስር በሠንጠረዥ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ይከፈታል።
7. /ሀ/ ሰነዱ የሚመረመርበት አድራሻ ሲ ኤም ሲ መንገድ መገናኛን አለፍ ብሎ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መ/ቤት በታች በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስትቲዩት አጠገብ ግብርና ሚኒስቴር ዋና መ/ቤት A ሕንጻ ላይ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 የግዥ ስራ አስፈፃሚ ስልክ ቁጥር 011-646-1242 ነው።
/ለ/ ሰነዱ ወጪ የሚሆንበት/የሚወሰድበት አድራሻ ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 7/ሀ/ ላይ የተገለጸው ነው።
/ሐ/ መጫረቻ ሰነድ የሚላክበት አድራሻ ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 7/ሀ/ ላይ የተገለጸው ነው።
/መ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 7/ሀ/ ላይ የተገለጸው ነው።
8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብ የሚያቀርቡት በወሰዱት ጨረታ ሰነድ ምዕራፍ 1 ክፍል 4 የተመለከቱትን ሰነዶች (ቅጾች) በመመላት ይሆናል።
9. ተጫራቾች የሚከተሉትን ሰነዶች/ማስረጃዎች አሟልተው ማቅረብ አለባቸው። ይህንን ያላሟሉ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ሊሆኑ ይችላሉ።
- ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ፤
- የግብር ግዴታ መወጣቱን በመግለጽ በዚሁ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚችል መሆኑን የሚገልጽ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ የጽሁፍ ማስረጃ፤
- ከብር 100,000 በላይ ዋጋ ባለው አገልግሎት የሚወዳደሩ ከሆነ የተ.እ.ታክስ (VAT) ሰርተፊኬት፤
- በመንግስት ግዥ ኤጄንሲው ድረ-ገጽ ለአቅራቢዎች ምዝገባ በተዘጋጀው ፎርም ላይ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ፣
- የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገባበት ፎርማት ተሞልቶ የተጫራቹ ድርጅት ፊርማና ማህተም የተደረገበት።
10.መስሪያ ቤቱ ጨረታውን መሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
ግብርና ሚኒስቴር
