የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ደረጃቸው የተጠበቁ የውስጥ ቁሳቁስ ፈርኒቸር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 0007/2015
የጋምቤላ ሕብ/ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ደረጃቸው የተጠበቁ የውስጥ ቁሳቁስ ፈርኒቸር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት -
- ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በመ/ቤቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (.አንድ መቶ ብር) በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በጋምቤላ ከተማ በሚገኘው የክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ቁጥር 14 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታhስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ ፊት በቅድሚያ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለሚጫረቱበት እያንዳንዱ ፈርኒቸር ዕቃዎች ዋጋ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የአቅራቢነት ወይም የአስመጪነት የምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የቢሮ የውስጥ ዕቃዎች ቁሳቁስ የሚያቀርቡበት ዋጋ ቫትን ጨምሮ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ዋናውን አንድ // እና የድርጅታቸውን ቁመና የሚገልፅ ሰነድ (Company profile) ፋይናንሻልና ቴhኒካል ኮፒ ሁለት /2/ በሰም በታሸገ በኤንቨሎፕ በማድረግ በ11ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ ከ 9፡00–9:30 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ አስገብተው በዚሁ እለት 9፡30 ሰዓት ላይ ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በቢሮው ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን መሪ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከማንኛውም ዓይነት ዕዳ ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 551 0037/0911 71 71 57 ይጠቀሙ።
የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መ/ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ
