የአዋሽ ጉምሩክ ቅጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ በኮንትሮባንድ መንገድ ወደ አገር ሊገቡ ሲሉ ይዞ የወረሳቸው የተለያዩ እቃዎች በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
የሀራጅ እና ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅጽቤት በተለያየ ጊዜ በኮንትሮባንድ መንገድ ወደ አገር ሊገቡ ሲሉ ይዞ የወረሳቸው የተለያዩ እቃዎች በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት ከታች በተገለጹ ቀናቶች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የጨረታ መስፈርቶች:
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራን (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክሰ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው
የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። - ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡00-6፡30 ቅዳሜ እስከ 3:45 የጨረታው ሰነድ ከአዋሽ ጉምሩh ቅ/ጽ/ቤት ገቢ አሰባሰብ ቢሮ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡት ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሐራጅ ጨረታ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በአዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።
|
ተቁ |
የጨረታ ቦታ
|
የጨረታው አይነት |
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች |
የዕቃዎች መመልከቻ ከወጣበት ቀን ጀምሮ
|
የጨረታው መዝጊያ |
|
1 |
አዋሽ ጉምክ |
ሀራጅ ጨረታ |
ብዛት ያላቸው ጫማዎች እና የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች |
ዓርብ መጋቢት እስከ 3:30 ሰዓት
|
ዓርብ መጋቢት እስከ 4:00 ሰዓት
|
|
2 |
የግልፅ ጨረታ |
ጫማዎች አልባሳት፣የመኪና መለዋወጫዎች፣የሞባይል ቀፎዎች፣ የኮስሞቲhስ እቃዎች እና ልዩ ልዩ እቃዎች
|
ቅዳሜ መጋቢት
|
ቅዳሜ መጋቢት
|
5. የጨረታው መከፈቻ ቦታ: በአዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሽነፋቸዉው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዘን ማውጣት ይኖርበታል።
8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
9.ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ለተጨማሪ መረጃ በስልh ቁጥር- 022-224-1402 ደውለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይቻላል።
የአዋሽ ጉምሩክ ቅጽቤት
