በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ.ቤ.ስ.ፅ 041/2015
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 01-
- ኤሌክትሮኒክስ (ላፕቶፕ ፣ ኮምፒውተር ፣ ፕሪንተር እና ዴስከ ቶፕ ኮምፒውተር) ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ስለተፈለገ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በዘርፋ የተሰማሩ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆን ይገባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ቡድን ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 19 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት
- ሎት 01-የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር) |አባይ ቤዚን ስስተዳደር ጽ/ቤት ስም በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማሰያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ እና በድርጅቱ ማህተም በተደረገበት ፖስታ እያንዳንዱ ፖስታው ላይ ተጽፎ ባህር ዳር በሚገኘው ብልጽግና ጽ/ቤት ጎን የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 15 ቀናት ከቀኑ 8፡00ሠዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅብዎታል።
- የጨረታ ሳጥኑ በአስራ አምስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ተወካዮች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት የሚከለክል አይሆንም።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ወይም ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከጽ/ቤቱ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 321 3144 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአባይ ቤዚን አስተዳደር ፅ/ቤት
ባህር ዳር
