አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ተሽከርካሪዎችን ፣ ማሽነሪዎች ፣ ሞባይሎችን ፣ የኤሌከትሮንክስ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳት እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልፅና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ. ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ የልዩ ልዩ ዕቃዎች እና ተሽከርካሪዎች ሽጭ ማስታወቂ የማስታወቂያ ቁጥር 38/2015
አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት የተተው የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን
- ተሽከርካሪዎችን ማሽነሪዎች፤
- ሞባይሎችን፣
- የኤሌከትሮንክስ ዕቃዎችን
- የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳት እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልፅና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል።
ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን።
በመሆኑም -
1. በቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን በጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ ለያ ቁጥር የተጨማሪ ዕሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼከ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሽግ ለጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ ከጨረታ አንድ ቀን በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።
2. የሚሸጠው ዕቃ ተሸከርካሪ ከሆነ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ በተ.ቁ 1 የተገለፁ ቅድም ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቮሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።
3. ተጫራቾች የግልፅ ጨረታውን ሠነድ ከሀሙስ መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን የሃራጅ ጨረታውን ደግሞ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት በነጻ ማግኘት ይችላሉ።
4. በግልፅ እና በሃራጅ በጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸዉ ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ለተሽከርካሪ ሀራጅ ጨረታ እና የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ እና ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) ተጫራቾች ማስያዝ አለባቸው።
6. ተጫራቾች በሚከተሉት የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታ መዝገያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት
|
|
1 |
አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት |
ሃራጅ |
እስከ 03/08/2015 |
መጋቢት 04/08/2015 4:00 ሠዓት ጀምሮ ይካሄዳል |
|
ግልፅ |
እስከ 04/08/2015 |
መጋቢት 05/08/2015 3:45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል |
7. የጨረታው መከፈቻ ቦታ-አአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
8 ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍለት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት ከተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
10. ከላይ በቁ.ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ዉስጥ ከፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረhቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
11. ጨረታውን በከፊልም ሆነ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ 011- 470 - 8503
አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
