Tender Detail

Tender Details

  • Deadline19 Apr 2023, 12:13 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ለአትክ/ፍራፍሬ መስኖ ውሀ አጠቃቀም ቡድን የሚያገለግል የማንጎ ዘር ከችግኝ ጣቢያ በጀት ላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ለአትክ/ፍራፍሬ መስኖ ውሀ አጠቃቀም ቡድን የሚያገለግል የማንጎ ዘር ከችግኝ ጣቢያ በጀት ላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል::

  1. ከሚፈለገው ዘር ጋር ተመሳሳይ የሆነ የታደሰና ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከ200,000 ብር/ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ሲኖርባቸው የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን የሚያካትትና የማያካትት መሆኑ መገለፅ አለበት። ይሄው ካልተገለጸና የቫት ሰርተፍኬት የአያያዙ ተጫራቾች ካሉ ግን ከነቫት የተቀመጠ ነው በማለት የምንወስድ መሆኑ መታወቅ አለበት።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ (ኦሪጅናል እና ኮፒ) በማለት ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው መሆን አለበት የሚያቀርቡት የማንጎ ዘር የክልሉ እጽዋት እና ሌሎች የግብ/ግብአቶች/ጥራት ቁጥጥር ኳራታይን ባለስልጣን ጽ/ቤት በክልሉ ውስጥ ከማንጎ በሽታ ነጻ ተብሎ ከተለየ አካባቢ እንዲቀርብ በሚያዘው ትእዛዝ መሰረት ማቅረብ የሚችልና ዘሩ ካለበት አካባቢ ከበሽታ ነጻ መሆኑን በደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
  7. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከደ/ጨ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ማግኘት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (CPO)ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
  9. የጨረታ ሳጥኑ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ጨ/ወ/ግ/ል/ጽ/ቤት በግ/ግብ/አቅ/ዝ/ፋ/አገ ቡድን ቢሮ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበአል/የእረፍት/ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን/ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ጨ/ወ/ግ/ል/ጽ/ቤት በግ/ግብ/አቅ/ገ/ፋ/አገ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ጨረታው በሚከፈትበት እለት ከቀኑ 8፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
  11. አሸናፊው ታውቆ የውል ማስከበሪያ 10% እንዲያስያዘና ከጽ/ቤቱ ጋር ውል ገብቶ እንደተፈራረመ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስለታል።
  12. አሸናፊው ማንጎ ዘሩን በደ/ጨ/ወ/ግ/ል/ጽ/ቤት በሚገኙ ችግኝ ጣቢያዎች ትራንስፖርቱን ችሎ የሚያደርስና ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል።
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደ/ጨ/ወ/ግ/ል/ጽ/ቤት በግ/ግብ/አቅ/ዝ/ፋ/አገ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 554 0672 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት

Save Tender