በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል Bummer Spare Parts በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/Re‐19/2015
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል Bumer Spare Parts በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 115.00 ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች በጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም C.P.O ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዢ መምሪያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው በዕለቱ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ይከፈታል።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ 011 442 02 16
ፋክስ 011 442 06 88
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
