Tender Detail

Tender Details

  • Deadline18 Apr 2023, 11:05 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Firewood

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ ፣ እንጦጦ የካ ፣ ጫንጮ እና ምስራቅ ሸዋ ዲስትሪክቶች (በምስራቅ ሸዋ ድስትሪክት ማህበራትና ድርጅቱ በጋራ የሚያስተዳድሩት) የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር OFWE/BA-06/2015

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ ፣ እንጦጦ የካ ፣ ጫንጮ እና ምስራቅ ሸዋ ዲስትሪክቶች (በምስራቅ ሸዋ ድስትሪክት ማህበራትና ድርጅቱ በጋራ የሚያስተዳድሩት) የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ እንጦጦ የካ እና ምስራቅ ሸዋ ዲስትሪክቶች (በምስራቅ ሸዋ ዲስትሪክት ማህበራትና ድርጅቱ በጋራ የሚያስተዳድሩት) የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም:

  1. የጊንዲላ ፣ የአጣና ፣ የእንጨት መሰንጠቂያ እና ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸዉ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል /ኦይል ሊቢያ/አጠገብ በሚገኘዉ የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ወይም ጨረታዉ የወጣበት ፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።
  2. ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወጣው ለ15 ተከታታይ ቀናት ለሁለተኛ ጊዜ የሚወጣው ለ10 ተከታተይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
  3. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቦታ ፣ ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ከሚገኙ ባንኮች በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (cpo) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 124 0249 መደወል ይችላሉ።

የኦሮሚያ ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት

Save Tender