የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች (ዴስክቶፕ ፣ ኮምፒውተር ፣ ላፕቶፕ ፣ ዩፒኤስ ፣ አንቲ-ቫይረስ እና Cisco Switch 24port) ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው አስመጪ እና አከፋፋይ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት
የቢሮ ዕቃዎች (Office Equipment) ግዥ ለመፈጸም
ግልጽ ጨረታ ቁጥር EMPDE/NCB/04/2014
ድርጅታችን ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች (ዴስክቶፕ፣ ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ዩፒኤስ፣ አንቲ-ቫይረስ እና Cisco Switch 24port) ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው አስመጪ እና አከፋፋይ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ነጥቦች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ፤ የተ.እ.ታ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢ ምዝገባ ሰርተፍኬት መሆኑን፡፡
- 2. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸትውን ሰነድ የማይመለሰ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ማከ|ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት 2፡oo ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 70,000.00 (ሰባ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው መስከረም 05 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡oo ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡oo ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግዴታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር -/011 646 3481 መረጃ ማገኘት ይቻላሉ ::
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት
