Tender Detail

Tender Details

  • Deadline31 Aug 2022, 12:09 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ከምባታ ጠምባሮ ዞን የዳምቦያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2015 ዓ.ም. የጽህፈት መሣሪያ (ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች) ፣ ተሽከሪካሪዎች ፣ ቋሚ ዕቃዎች ፣ ፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ዳ/ወ/ፋ/0004/2015 ዓ.ም.

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ከምባታ ጠምባሮ ዞን የዳምቦያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2015 ዓ.ም. በወረዳው ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች የቢሮ አላቂ ዕቃዎችን፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን ፈርኒቸሮችን ኤሌክትሮኒከስ እና ሞተር ሳይከሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት (1) የጽህፈት መሣሪያ/ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት (2) ተሽከሪካሪዎች
  • ሎት (3) ቋሚ ዕቃዎች ፈርኒቸር
  • ሎት (4) ኤሌክትሮኒክስ

የጨረታ መለያ ቁጥር /ዳ/ወ/ፋ/0004/2015 ዓ.ም.

በመሆኑም፡_

  1. ከላይ በተዘረዘሩ ሎቶች በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
  3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
  4. የቫት ተመዝጋቢነት ምዝገባ ምስክር ሰርተፍኬት ያለው
  5. የመንግሥት ግዥ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስhር ወረቀት ያለው
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በየዘርፉ ብር 10000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) በጥሬ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ የሚችል።
  7. ያሸነፈውን ዕቃዎች እስከ ዳምቦያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል።
  8. ተጫራቾች ቴክኒኩን ለብቻው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ የሚችሉ። ማንኛውም ከላይ ከተራ-ቁጥር 1-8 የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟላ ተጫራች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ በ30 ቀናት ውስጥ የዕቃውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ከዳምቦያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ከቢሮ ቁጥር- 03 የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመከፈል መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች ዋጋውን በአንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በየግሉ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዳምቦያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር- 03 ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 31ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።ጨረታው በ31ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን 8፡30 ላይ ተጨራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተጫራቹ ወይም የተወካዩ ያለመገኘት የጨረታውን የአከፋፈት ሂደት አያስተጓጉልም።

መ/ቤቱ የተሻለ ኣማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0910 32 65 79 / 0945 88 33 71/0916 39 12 35

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ በከምባታ ጠምባሮ ዞን

የዳምቦያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት

Save Tender