በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወርሐ የካቲት የመ/ጀ/ደ/ት/ቤት በ2015 ዓ.ም. የበጀት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወርሐ የካቲት የመ/ጀ/ደ/ት/ቤት በ2015 ዓ.ም. የበጀት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች
- አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
- አላቂ የሕክምና ዕቃዎች
- ህትመት ፣
- ልዩ ልዩ ጥገናዎች ፣
- ልዩ ልዩ መሣሪያዎች ፣
- ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች ፣
- ቋሚ ዕቃዎች፣
በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ ስሚፈልጉ :
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ ዕሴት (VAT) ተመዝጋቢነት ማስረጃ መቅረብ የሚችል ፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚለስ ጠቅላላ ዋጋ ብር 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ መያዣ (CPO) ማቅረብ የሚችል።
- የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10ተከታታይ የሥራ ቀናት በወርሐ የካቲት የመጀ/ደ/ትቤት ፋይናንስ ቢሮ በግንባር በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው ።
- የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል ብሎ በመለየት በተለያየ ፖስታ አሽገው ሲያመጡ ሲፒኦውን (CPO) እና ተያያዥ መረጃዎችን
- ተጫራች የሚጫረቱበትን ዋጋ በዝርዝር ሰነድላይ ባለው ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በፋይናንስ ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት በ10ኛው ቀን ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። በ11ኛው ቀን ዕለቱ በአል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊ ጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና ማስያዝ አለበት።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- አድራሻ
- ቄራ በርታ ኮንስትራከሽን ከፍ ብሎ ወደ ቂርቆስ መሄጃ መንገድ ላይ።
- በላንቻ በኮንኮርድ ገባ ብሎ ወረዳ 04 ጽ/ቤት አለፍ ብሎ በስተግራ ባለው አስፓልት መንገድ አብዮት ቅርስ መሰናዶ ት/ቤት ከፍ ብሎ ወደ ቄራ መውጫ ላይ ይገኛል።
ስልክ ቁጥር 011 470 3795/ 011 470 3789
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወርሐ የካቲት የመ/ጀ/ደ/ት/ቤት
