የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን በቦኬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለወረዳው የተለያዩ መ/ቤቶች የሚውል አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ተ.ቁጥር 2/03/MWD/2015
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን በቦኬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለወረዳው የተለያዩ መ/ቤቶች የሚውል አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ዕቃውን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁም ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ ) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰዱን በማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በቦኬ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በመንግስት መ/ቤት የስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም መሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይችልም።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 11/01/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 8:00 ሰዓት ድረስ ለተጫራቾች ክፍት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርገው እስከ 11/01/2015 ዓ.ም. 8:00 ሰዓት በቦኬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ ቤት ቢሮ ቁ.2 ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ እለት ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- አሸናፊ ድርጅት/ተጫራቹ /ያሸነፈበትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ቦኬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የተፈለገውን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- በሽያጭ የቀረበው ዕቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ነጋዴው / አሸናፊ ድርጅቱ/ በራሱ ወጪ ዕቃውን የመለወጥ ወይም ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ አለበት።
- የዕቃውን ማስጫኛና የማውረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርገው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን በቦኬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
ቦኬ ጢቆ
ሞባይል 0912872285/0911369861
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን በቦኬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
