Tender Detail

Tender Details

  • Deadline07 Sep 2022, 11:34 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ኮር አይ-5 ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ፣ የተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ባለ 50 ገጽ እና እስክሪቢቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2015

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ  ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ኮር አይ-5 ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ፣ የተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ባለ 50 ገጽ እና እስክሪቢቶ ግዥ በ2014 ዓ.ም. በዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 በዚህም መሰረት በግልጽ ጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ፡፡

  • ሎት1. ኮር አይ-5 ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ግዥ
  • ሎት2. የተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ባለ 50 ገጽ እና እስክርቢቶ ግዥ
  1. የዕቃና የአቅርቦት አገልግሎት ዝርዝር ላይ የተመዘገበና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  2. የዘመኑን የ2014 ዓ.ም. ግብር የከፈሉና የ2014 ዓ.ም. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ሆኖ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ማረጋገጥ የምስክር ወረቀት /VAT/ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር/ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የግልጽ ጨረታ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ኦርጂናልንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ግልጽ ጨረታው እንዲሳተፉ ከተጋበዙበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀን 8:00 ድረስ ለዚህ ግልጽ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን በ/ቤ/ክ/መ/ትም/ቢሮ ቁጥር 8 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. በግልጽ ጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ከተጋበዙበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ልክ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8:30 ላይ ይከፈታል። ቀኑ ቅዳሜ /እሁድ/ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  6. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርበት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡
  7. ተጫራቾች የጨረታውን መሉ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ብር 100 የማይመለስ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀን ቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልል መንግስት ት/ሮ ቢሮ ቁጥር 08 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  8. አሸናፊው ድርጅት የላፕቶፕ ኮምፒዩተሩን እና የተማሪዎች የመማሪያ ባለ 50 ገጽ ደብተር አሶሳ በ/ቤ/ጉ/ክ/መ/ትም/ቢሮ ግቢ ድረስ በራሱ ትራንስፖርት በማምጣት የማስረከብ ግዴታ አለበት።
  9. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታው መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ባይገኙ የግልጽ ጨረታውን ሂደት አያስተጓግልም::
  10. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ግልጽ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0577752979 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ቤ/ጉ/መ/ት ቢሮ የግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት

አሶሳ

Save Tender