በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ የተደረጉ ተሽከርካሪ ፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አልባሳት እና ኮስሞቲክስ በግልፅ ጨረታ እንዲሁም ተሽከርካሪ በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 02/2015
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ የተደረጉ ተሽከርካሪ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አልባሳት እና ኮስሞቲክስ በግልፅ ጨረታ እንዲሁም ተሽከርካሪ በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ እንፈልጋለን።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መመሪያ የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ።
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ አለበት። ለተሽከርካሪዎች ማንኛውም ከ18 አመት በላይ የሆነው መጫረት ይችላል።
- በተጠቀሰው መስፈርት በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
- የጨረታ ሰነድና መመሪያ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ለመግዛት ለግልጽ ጨረታ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመግዛት መወዳደር ይችላሉ ።
- የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች በጨረታው ሊሳተፍ አይችልም። እንዲሁም በኮፒ የጨረታ ሰነድ መጠቀም አይችልም።
- ተጫራቾች ለግልጽ ጨረታ የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሃራጅ ጨረታ 50,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው። አሸናፊ ለሆኑት የጨረታ ማስከበሪያው በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ የሚታሰብ ይሆናል። ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ ያስያዙት ቼክ (CPO) ተመላሽ ይሆናል።
- ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ መጨረሻ (ግርጌ) ላይ የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የዕቃዎች የጨረታ መነሻ ጠቅላላ ዋጋን በመንተራስ ሲሆን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ ተጫራቹ መፈረም አለበት።
- ተጫራቾች ለውድድር የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ሳይጨምር ሆኖ ነገር ግን የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) 15% ተጨማሪ እንደሚሆን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም። ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት (እቃው በሚገኝበት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ቢሮ) ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም።
- ሁለት ተጫራቾች ለአንድ እቃ እኩል ዋጋ በመስጠት አሸናፊ ቢሆኑ እንደገና በማወዳደር አሸናፊው እንዲለይ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር አይነትና ብዛት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማየት የሚቻል ሲሆን ጨረታው የሚከናወነው በስምንተኛው ቀን ለግልጽ ጨረታ 3፡45 ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን የሃራጅ ጨረታው 8፡00 የሚጀመር ይሆናል ። ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ መውጣት አይችሉም። ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ውጤት እስከሚገለፅ ድረስ ጸንቶ ይቆያል።
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ05 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል።
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የሰነድ መግዣ ቦታ በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገቢ ሂሳብ ቡድን ቢሮ ቁጥር 103 ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0335510693 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
