የምሻ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት የጽህፈት መሣሪያዎች እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በሀዲያ ዞን የምሻ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዓይነት
- ሎት.1. የጽህፈት መሣሪያዎችን
- ሎት. 2.ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ
በዚህ መሠረት ተወዳዳሪ ተጫራቾች
- በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
- የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው ድርጅቶች
በሀዲያ ዞን የምሻ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ከግዥ/ፋ/ን/አስ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በአካል በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 50(ሃምሳ ብር) በመክፈል እንድትገዙና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሎቶች 5000/ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚጠበቅባቸው እና የጨረታውን መወዳደሪያ ዋጋ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ኦርጅናል እና ኮፒ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 16 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡና ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0910454656 /0916673483 /0954497793 መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በሀዲያ ዞን የምሻ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
