የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ግሬደር ፣ ሮለር ፣ ዶዘር እና እስካቫተር የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር፡ሲ/መ/ባ/001/2015
የማሽነሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2015 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የመንገድ ግንባታ ሥራ ለማሠራት
- 15 (አሥራ አምስት) ግሬደር ፣
- 15 (አሥራ አምስት) ሮለር ፣
- 5(አምስት) ዶዘር እና
- 7 (ሰባት) እስካቫተር የኮንስትራክሽን ማሸነሪዎችን መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት:
- ተጫራቾች አግባብነት ያለውን ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚያሳይ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር -5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ(CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (unconditional Bid) የእያንዳንዱ ማሽኖች የጠቅላላውን ዋጋ 1% ሆኖ ከ500,000 ብር በላይ የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000 ብቻ CPO ወይም ባንክ ጋራንት ለማሰራት ለየብቻው በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- የሚቀርቡ ማሽነሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው ፣ የስሪት ዘመናቸው እና ሌሎች መጫረቻ ሰነዱ ላይ የተገለጹ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
- የሚቀርቡ ማሽነሪዎች ወደ ሥራ በሚሰማሩበት ጊዜ እና ከአንዱ ፕሮጀክት ወደ ሌላ ፕሮጀክት ማሽነሮችን ማንቀሳቀስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አሸናፊው ድርጅት በራሳቸው ወጪ አጓጉዘው ወጪውን በባለስልጣኑ መ/ቤት የሚሸፈን ይሆናል።
- የሚቀርቡ ማሽነሪዎች የኢንጂን ሠዓታቸው እና የነዳጅ ኦዲዮ ሜትር በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት።
- ከዚህ በፊት ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ ተሰቶት ማሽነሪዎችን ወደ ስራ ያላስገባና ውላቸው የተቋረጠ የማሽነሪ አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ እና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ከላይ የተጠቀሰው ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
- በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማክበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገጽ ላይ ማህተምና ፊርማ ያለማድረግ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ያለበት የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራች ድርጅት የሚያቀርበው ማሽን ባለቤትነት ሊብሬ ወይም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር:-046 212 8446
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን
ሐዋሳ
