የፈረንሣይ ጉራራ ምስራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነምሕረት እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት የቤተክርስቲያን ይዞታ እና ንብረት የሆነውን ባዶ ቦታዎች በተጓዳኝ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የፈረንሣይ ጉራራ ምስራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነምሕረት እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በጸበል ቦታው አካባቢ የሚገኘውን የቤተክርስቲያን ይዞታ እና ንብረት የሆነውን ባዶ ቦታዎች በተጓዳኝ ለተለያየ የልማት አገልግሎት ለማዋል ሕጋዊ መሥፈርቱን ለሚያሟሉ አካላት (ድርጅቶች) በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
ሀ) መሥፈርትን በተመለከተ
1. የኢ.ኦ.ተ. ቤተክርስቲያን እምነት እና ስርአት የሚያሟላ፣
2. የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ያለው (ኮፒ ማቅረብ የሚችል)፣
3. የንግድ ፈቃድ ያለው (ኮፒ ማቅረብ የሚችል)፣
4 የሥራ ዘርፍን በተመለከተ ከቤተክርስቲያን ሥርአት ውጪ ያልሆነ ሥራ የሚሰራበት፣
ለ) ጨረታው ከፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ ከነሐሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. 2:30 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ይሆናል።
ሐ) ለጨረታ የቀረበውን ቦታ በተመለከተ በቅድሚያ ቦታውን በጉራራ ምስራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነምሕረት እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የጸበል ቦታ በአካል በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በደብሩ የዕለት ገንዘብ መቀበያ ቢሮ በመገኘት የጨረታ ሰነድ መግዣውን ገንዘብ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በገቢ ሞዴል በመክፈል ከደብሩ አስተዳደር የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ዝርዝር ገንዘብ መቀበያ ቢሮ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይቻላል።
መ) የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በደብሩ የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ በታሸገ ፖስታ ሳጥን ውስጥ እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ግዴታ ነው።
ሠ) የጨረታው የመከፈቻ ቀን ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የሚመለከታቸው ሁሉ በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
ረ) ጨረታውን የሚሳተፉ አካላት ቅድሚያ የጨረታ ማስከበሪያ በዕለቱ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በደብሩ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ሰ) ደረጃው እና የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር
ሀ/A 1ኛ ደረጃ የቦታው ሥፋት በካሬ ሜትር 280 m2
ለ/B 2ኛ ደረጃ 280 m2 ፤ ሐ/C1ኛ ደረጃ 396 m2 መD2ኛ ደረጃ 396 m2፤ ሠ/E 1424 m2 ፤ ረ/F 2646 m2 ጠቅላላ ለጨረታ የቀረበው የቦታ ስፋት 568o m2
የልማት አገልግሎት መለጫ ሥፍራው እና ታሳቢ የተደረጉ የአገልግሎት አይነቶች እና ሁለገብ አማራጮች የሚከተሉት ናቸው።
ለብረታ ብረት ሥራዎች ወይም ሁለገብ፣ ለእንጨት ሥራዎች ወይም ሁለገብ፣ ለጎጆ ኢንዱስትሪ ወይም ሁለገብ፣ ለጎጆ ኢንዱስትሪ ወይም ሁለገብ፣ ለመጋዘን ወይም ሁለገብ እና ለትምህርት ቤት
ማሳሰቢያ፡-
1. ለጨረታው አሸናፊ ውል በ 1ወር ጊዜ ውስጥ ይፈጸማል ነገር ግን የጨረታው አሸናፊ በ 1 ወር ጊዜ ውስጥ በደብሩ ተገኝቶ ውሉን ካልፈጸመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም።
2- የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡-0911 69 40 54
+251 11 812 2498
0977 90 62 95
በኢ.ኦ.ተ. ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፈረንሣይ ጉራሪ ምስራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነምሕረት እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት
