የሶዶ-ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት ንጹህ የመጠጥ ውሃ መስመር ዝርጋታ አገልግሎት የሚውል እስከ 4000 ሜትር ርዝመት የሚደርስ የፕላስቲክ-ትቦ/HDP2” የውጪውን/ ቨርጂን ታይፕ ሆኖ ባለ ፒ.ኤን-16 እና ፒ.ኤን-10 ዓይነት መግዛት ይፈልጋል
የፕላስቲክ ትቦ/HDP 2'' አቅርቦት/ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ በድጋሚ የወጣ
የሶዶ-ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት በዘላቂ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ለህብረተሰብ ንጹህ የመጠጥ ውሃ መስመር ዝርጋታ አገልግሎት የሚውል እስከ 4000 ሜትር ርዝመት የሚደርስ የፕላስቲክ-ትቦ/HDP2” የውጪውን/ ቨርጂን ታይፕ ሆኖ ባለ ፒ.ኤን-16 እና ፒ.ኤን-10 ዓይነት መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች የምታሟሉና በሽያጭ ማቅረብ የምትችሉ በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ።
- አሸናፊው ሻጭ /አቅራቢ ዕቃውን በተፈለገው ጊዜ እስከ ድርጅታችን ድረስ አጓጉዞ በማቅረብ አስረክቦ ሲያጠናቅቅ የአሸነፈበትን አጠቃላይ ዋጋ ሕጋዊ ደረሰኝ በማቅረብ ክፍያውን ይረከባል'ተገቢው የመንግስት ታክስም ተቀናሽ ይሆናል።
- ተጫራች ለጨረታው የሚያቀርበውን የጠቅላላ ዋጋ 1% ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- ተጫራቹ ይህ ጨረታ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዕቃውን የምትሸጡበትን የአንዱን ሜትር ዋጋ በድርጅታችሁ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ በ7 (ሰባት) ተከታታይ ክፍት የስራ ቀናት ውስጥ በታሸገ ኢንቨሎፕ ቡኢ ከተማ በሚገኘው የድርጅታችን ቅጥር ግቢ ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታዉ ሳጥን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው የስራ ቀን (ማለትም ነሀሴ 19/2014 ዓ.ም.) ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል።
- የጨረታው ሳጥን የሚከፈተዉ በድርጅታችን ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸዉ በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው ክፍት የስራ ቀን (ማለትም ነሀሴ 19/2014 ዓ.ም.) ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይሆናል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የትጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሶዶ ቡኢ የህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት ቡኢ ከተማ “ሶዶ ወረዳ' ጉራጌ ዞን ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ-ምዕራብ አቅጣጫ 103 ኪ.ሜ. በአለምገና-ቡታጅራ/ሆሳና ዋናው አስፋልት መንገድ።
የስልክ ቁጥር፡ 046 883 0266 ወይም 046 883 0265 ወይም 046 883 0350 ወይም 046 883 0023
