Tender Detail

Tender Details

  • Deadline06 Aug 2022, 10:22 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Water System Installation

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዲዛይን-ግንባታ የውሃ ምንጭ ጥናት ፣ ምርመራ ፣ ቁፋሮ ፣ ልማት እና የፓምፕ ሙከራ እና የፓምፕ እና የቧንቧ መስመር ዝርጋታ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ቅጥር ግቢ ውስጥ ለማሰራት ብቁ ተወዳዳሪዎችን ለመጋበዝ ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T325

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዲዛይን-ግንባታ የውሃ ምንጭ ጥናት፣ ምርመራ፣ ቁፋሮ፣ ልማት እና የፓምፕ ሙከራ እና የፓምፕ እና የቧንቧ መስመር ዝርጋታ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ቅጥር ግቢ ውስጥ ለማሰራት ብቁ ተወዳዳሪዎችን ለመጋበዝ ይፈልጋል። የፕሮጀቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ በ210 የቀን መቁጠሪያ ቀናት ውስጥ ይሆናል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች፣ አስፈላጊውን የሰው ሃይል፣ ማሽንና የግንባታ ግብዓት ማሟላት የሚችሉ ሥራ ተቋራጮች ስራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ ለመስራት ለ2014 ዓ.ም ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
  2. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ 2014 ዓ.ም የታደሰ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GWWC-2 and above)
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
  4. የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታከስ እዳ ነጻ ስለሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
  5. የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  6. ተጫራቾች በአማካሪ ድርጅት ለሚያሰሩት ሥራ የተፈረመ ውል ተያይዞ መቅረብ አለበት። አማካሪ ድርጅቱ ለ2014 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የተሻሻለ የብቃት/ምዝገባ ምድብ-2 የምከር አገልግሎት በከርሰ ምድር ውሃ ምርመራ እና ተዛማጅ መስኮች ፍቃድ እና የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት መቅረብ ይኖርበታል።
  •  ጨረታው የሚካሄደው በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ (NCB) አሰራር ነው። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባን ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር/አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ
    ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T325 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላh የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
  • በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት(ስራ) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት ኣይኖረውም። ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴhኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍል እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፓስ ቢሮ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ
ዒትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-4552

ኢሜይል:: BirtukanS@ethiopianairlines.com 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ ብቱ የተጠበቀ ነው።

 

Save Tender