በምዕ/ጐ/ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ. ነጭ በቆሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕ/ጐ/ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ. 24000 (ሃያ አራት ሽህ) ኩ/ል ነጭ በቆሎ ቡሬ ከተማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም
- በጨረታው ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን አለበት።
- ማንኛውም ተጫራቾች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ ሲሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፓስታ ውስጥ በማስገባት ማስያዝ አለበት።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100 ብር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩንየኑ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 8 የስራ ቀናት አየር ላይ ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዳችው ዪኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በ8ኛው ቀን 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል። ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አይስተጓጎልም።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት። ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
- የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እንዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት።(ተወካይ ከሆነ የውክልና ደብዳቤ ማያያዝ አለበት)።
- የማንሻ ወይም ሰብሉን አንስቶ የሚጨርስበት ጊዜ 45 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል።
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል።
- የማስጫኛ እና ሌሎች ወጭዎችን ገዥ የሚሸፍን ይሆናል።
- ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0587 74 06 40/10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ።
የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ.
