የአዲስ ዘመን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለወፍጮና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የፓምፕ ሞተር ዲናሞ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አዘመ 74/309/736
የአዲስ ዘመን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለወፍጮና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የፓምፕ ሞተር (ዲናሞ) ብዛት አራት ፍላጎት ላላቸው ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 10 የማይመለስ ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ብር 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ በጽ/ቤቱ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡት ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበው ሰነድ ቅደም ተከተል መሰረት ቫትን ጨምሮ ይሆናል።
- ጨረታው 17/12/2014 ዓ.ም. 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከቀረቡት ሞተሮች/ዲናሞዎች ውስጥ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918095872 | 0918048058 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ ዘመን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
