የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የአንደኛ ዙር ግዥ በ2015 የበጀት ዓመት በዞን ደረጃ ለሚገኙ መ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ የቢሮ ውስጥ መገልገያዎች ፣ የጽዳት ዕቃዎች ፣ የመኪና ጎማዎች ፣ ልዩ ልዩ ፈርኒቸሮች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታቂያ ቁጥር 001/2015
የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የአንደኛ ዙር ግዥ በ2015 የበጀት ዓመት በዞን ደረጃ ለሚገኙ መ/ቤቶች
- የጽህፈት መሳሪያዎች ፣
- የቢሮ ውስጥ መገልገያዎች ፣
- የጽዳት ዕቃዎች ፣
- የመኪና ጎማዎች ፣
- ልዩ ልዩ ፈርኒቸሮችና
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዛት ይፈልጋል
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
- የቫት ተመዝጋቢ ሆነው የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ የሚያቀርቡ እንዲሁም የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ ጨረታዎች ላይ ለመወዳደር እንዲችሉ የተፈቀደላቸው እና ክሊራንስ ከሚለከተው መንግስታዊ አካል ማቅረብ የሚችሉ ሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ከሰ/ሸ/ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ / ባንክ በተረጋገጠ /ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት የዋስትና ደብዳቤ ከአደራጃቸው አካል ለሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በማስፃፍ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን በዞናችን ሦስት ጊዜ እና ከዚያ በላይ የተወዳደሩ ማህበራት በባን በተረጋገጠ /ሲ.ፒ.ኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ሞልተው በታሸı ኤንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የገዙትን ሰነድ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ 16ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን በ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ሰኞ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዝ የማስጫንና የማውረድ ወጪን መቻል ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 135 3114 በመደወል እንዲሁም ሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ቀርበው መረዳት ይችላሉ።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክስላዊ መንግስት መስተዳደር የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ጽ/ቤት
ፍቼ
