ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃላ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ ልዩ ልዩ እቃዎችን መሸጥ ይፈልጋል
የልዩ ልዩ እቃዎች የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2014
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃላ/የተ/የግ/ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ልዩ ልዩ ዕቃዎች
- የብረት በርሚል
- ካሳ የተከፈለባቸው ጐማዎች ያገለገሉ ብላደሮች
- ልዩ ልዩ ዕቃዎች
- ያገለገለ ዘይት ፣ የፈርነስ ፍሳሽ
- ልዩ ልዩ የኮርድ ክሮች
- ልዩ ልዩ ስኮርች ኮምፓውንዶች
- ስክራፕ እና አገልግሎት ሰጥተው የተመለሱ የተቆረጡ ጎማዎች በመሆኑም ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በሙሉ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ከኩባንያው የምርት ሽያጭ ቢሮ መግዛት እና እቃዎቹን ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጓቸውን እቃዎች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ በግልፅ ሞልተው ፣ ሙሉ ስማቸውን ጽፈው ከፈረሙበት በኋላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሽያጭ ቢሮ ፊት ለፊት ባለው የጥበቃ በር ቁጥር 2 ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ሣጥኑ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡05 ሰዓት ይታሸጋል።ጨረታው ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡20 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ:-ንብረት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ
ስልክ ቁጥር 011-442-1555/249 ወይም 0943 88 03 72 መጠየቅ ይቻላል።
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃላ/የተ/የግ/ማ
