Tender Detail

Tender Details

  • Deadline19 Aug 2022, 10:47 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Printed Advertising Materials

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል በፑል አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ለ2015 በጀት አመት የሚያስፈልጋቸውን የተለያዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር 001/2015

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል በፑል አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ለ2015 በጀት አመት የሚያስፈልጋቸውን

  • ሎት1. አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣
  • ሎት2. ቋሚ የቢሮ እቃዎች(ፈርኒቸር) ግዥ ፣
  • ሎት3. ኤሌክትሮኒክስ የቢሮ እቃዎች ግዥ ፣
  • ሎት4. የጽዳት እቃዎች ፣
  • ሎት5. የደንብ ልብስ ግዥ ፣
  • ሎት6. የህዝብ አውቶቢስ አገልግሎት ኪራይ ግዥ ፣
  • ሎት7. ታክሲና አይሱዙ ኪራይ አገ/ት ግዥ ፣
  • ሎት8. ኤሌክትሮኒክስ የቢሮ እቃዎች ጥገና ግዥ ፣
  • ሎት9. የጉልበት ስራተኛ አገ/ት ግዥ ፣
  • ሎት10. የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ፣
  • ሎት11. የህትመት ውጤቶች አገ/ት ግዥ ሲሆኑ ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ፣  በአቅራቢነት የተመዘገቡና በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የሚያስረዳ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ለታክሲ ኪራይ አገ/ት እና የህዝብ አውቶቡስ አገ/ት ለማቅረብ የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች በስማቸው የተመዘገበ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ
    • ሎት1. አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ ብር 10,000 ፣
    • ሎት2. ቋሚ የቢሮ እቃዎች (ፈርኒቸር) ግዥ ብር 300,000 ፣
    • ሎት3. ኤሌክትሮኒክስ የቢሮ እቃዎች ግዥ ብር 30,000 ፣
    • ሎት4. የጽዳት እቃዎች ብር 5,000፣
    • ሎት5. የደንብ ልብስ ግዥ ብር 5,000፣
    • ሎት6. የህዝብ አውቶቢስ አገልግሎት ኪራይ ግዥ ብር 5,000 ፣
    • ሎት7. ታክሲና አይሱዙ ኪራይ አገ/ት ግዥ ብር 5,000፣
    • ሎት8. ኤሌክትሮኒክስ የቢሮ እቃዎች ጥገና ግዥ ብር 10,000 ፣
    • ሎት9. የጉልበት ሰራተኛ አገ/ት ግዥ ብር 5,000 ፣
    •  ሎት10.የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ብር 5,000 ፣
    • ሎት11. የህትመት ውጤቶች አገ/ት ግዥ ብር 10,000 ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያውን ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ) በመክፈል 5ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦሪጂናልና ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማደራጀት ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የክፍለ ከተማው ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በሚገኝበት ሀይሌ ጋርመንት አደባባይ በሚገኘው የአስተዳደሩ ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ11፡3o ሰአት ታሽጎ በማግስቱ በ11ኛው ቀን 4፡30 ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች ጨረታው አስቸኳይ ስለሆነ የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት 1 ፣ 2 ፣ 3 ፣ 4 ፣ 5 እና 11 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ሌሎች ናሙና ያልተጠየቀባቸው ሎቶች ሎት 6 ፣ 7 ፣ 8 ፣ 9 እና 10 ግን በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ወይም የአገልግሎት ግዥ ለእያንዳንዱ እቃ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
  8. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም ።
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 በተጨማሪ ለማብራሪያ ጥያቄ ::

አድራሻ ሀይሌ ጋርመንት ላፍቶ አደባባይ በሚገኘው የአስተዳደሩ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 የን/ስ/ላ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን

ስልከ ቁጥር 0118-83-80-20

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን

Save Tender