Tender Detail

Tender Details

  • Deadline22 Aug 2022, 10:39 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ በ2015 በጀት ዓመት የምግብ ጥሬ ዕቃዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል



ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ በ2015 በጀት ዓመት ሎት 1 የምግብ ጥሬ ዕቃዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ጋር የሚፈልጉ መስፈርቶች፤

  • ለዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ
  • የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት
  • የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ
  • የአቅራቢነት ማስረጃ
  • የግብር ከፋይነት መለያ TIN ቁጥር
  1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ ፋይናንስና በጀት አስ/ር ቢሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ ብር ብቻ በመፈል ይህ ጨረታ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
  2. ከተሰጠው መስፈርት ወይም የቴኒክ ፍላጎት መግለጫ ውጭ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ። ተጫራቾች እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ አሸናፊው በዕጣ የሚለይ ይሆናል።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
  4. በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር የተገለጹትን ዕቃዎች ዓይነት የማቅረቢያ ጊዜ በውል ስምምነት የሚገለጽ ሆኖ አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን የአገልግሎት ዓይነት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ ግቢ ውስጥ የአገልግሎቱን ስምምነት መፈጸም አለበት።
  5. ተጫራቾች ሎት 1 የምግብ ጥሬ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ሌተር| ደብዳቤ| በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ ስም አዘጋጅተው ለብቻው በፖስታ በማሸግ ከኦሪጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የአገቱን ዝርዝር ነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ ተደርጎ በተሰጠው አiት ግዥ ዝርዝር ላይ በመሙላትና የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ በማሳረፍ 1አንድ ኦሪጅናልና 2 (ሁለት) ፎቶ ኮፒ በማድረግ ግዥና ንብረት አስ/ር ቢሮ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ16/12/ 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡15 ላይ ታሽጎ ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30ይከፈታል። የተጫራቾቹ ወይም የወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት ያስተጓጉልም።
  7. የጨረታው ውጤት ጨረታው ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ / በፋስ / በስልክ እና በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።
  8. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ሥራ አፈጸጸም ዋስትና (ውል ማስከበሪያ ) በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. ማንኛውም ተጫራች በውል ውስጥ የተካተቱትን ሕጎች ማበር አለበት።
  10. ካምፓሱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0916 726 033 / 0908 90 42 39 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
ዋቶሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ

/ዱራሜ/

Save Tender