በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን 65 kVA genertor ፣ Cisco 4000 Series routers ፣ conditioner እና SFP moudule በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን ለሴንትራላይዜሽን ዝርጋታ የሚያስፈልጉ እቃዎችን ማለትም 65 kVA genertor ፣ Cisco 4000 Series routers ፣Air conditioner እና SFP moudule በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- በዘርፉ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር ) በመክፈል በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቁጥር 220 ማግኘት ይችላሉ።
- ለሴንትራላይዜሽን ዝርጋታ የሚያስፈልጉ እቃዎችን ማለትም SFP moudule፣10KVA genertor ፣Cisco 4000 Series routers and Air conditioner ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽ)
ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል። - አሸናፊ ድርጅት የሚለየው በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ሞልቶ ያቀረበ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን እና ቴክኒካል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ፋይናንሽል እና ቴክኒካል ብሎ ፖስታው ላይ በመፃፍ ሁለቱን በአንድ ፖስታ አሽጎ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 308 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እሰከ ነሃሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቁጥር 308 ነሃሴ 17ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሸጐ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 308 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 6427 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአብክመ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን
